ሚንበር ቲቪ ሚንበር መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ወደ ህዝብ ከሚያደርሳቸው ሥራዎቹ አንዱ ሲሆን አየር ላይ በዋለ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ቅቡልነትን በማትረፍ በዘርፉ ከሚጠቀሱ ጣቢያዎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ የቴሌቪዥን ቻናል ነው፡፡

ራዕይ
ጥራት እና ጥበባዊ ፈጠራን መለያቸው ያደረጉ ሚዲያ ውጤቶችን አምርቶ ለህዝብ በማቅረብ በምስራቅ አፍሪካ ሁለንተናዊ ከፍታን የሚያመጣ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሆኖ መገኘት!

ዓላማ
የመገናኛ ብዙኃን ውጤቶችን በመጠቀም የኢስላምን ብሎም የሃገራችን ውብ ገጽታ ለዓለም ማስተዋወቅ!
– ጥራት ያለው አገልግሎት አሰጣጥን ለማዳበር በመስኩ የበቁ ሙያተኞችን ማፍራት!
– የማህበረሰባችንን እሴቶችና መልካም ባህሎች ጠብቆ ለማቆየት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የጎላ ተሳትፎ ማድረግ!
– የደንበኞቻችን ፍላጎት ያማከለ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠትና ጤናማ የሥራ ግንኑነት በማስፈን ትርፋማ ሆኖ መገኘት!
– ስለ እስልምና ለሌላው ማኅበረሰብ በጥበብ በማስተማር፤ ልዩነቶችን ባከበረ መልኩ ማቀራረብ!

ተልዕኮ
በፈጠራ የታገዘና በጥራቱ የላቀ አገልግሎት በመስጠት የደንበኞችን ፍላጎት ማርካት!

በአሁኑ ሰዓት የሚንበር ቲቪ ስርጭት በመላው ዓለም
በኢትዮ-ሳት በፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል በመተላለፍ ላይ ይገኛል፡፡